የነቀምቴ ጉዲና ቱምሳ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ የበረራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።
የአይሮፕላን ማረፊያው የበረራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የተካሄደው የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲን ጨምሮ የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው።
በ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ የምሥራቅ ወለጋ ዞን መዲና በሆነችው ነቀምቴ የተገነባው ጉዲና ቱምሳ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያው በረራ መጀመር የረጅም ዓመት ጥያቄያቸው ምላሽ የሰጠ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች በደስታ ገልጸዋል።
የአይሮፕላን ማረፊያው በነቀምቴ መገንባት አካባቢው የሚታወቅበትን የቡና እና ፍራፍሬ ምርቶችን በቀላሉ ለማዕከላዊ ገበያና ለውጭ ገበያ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚረዳም ተገልጿል።
ምንጭ፦ ኢዜአ