አየር መንገዱ አህጉራዊ የካርጎ አገልግሎት ሽልማቶችን አገኘ

የኢትዮጵያ የካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን ሁለት ሽልማቶችን ማግኘቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አስታወቀ።

“Aviation Achievement Awards” የተሰኘ የአቪዬሽን ዘርፍ የሽልማት መርሃ ግብር በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዱባይ ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የህክምና ቁሳቁሶችን በማጓጓዝ እና አጠቃላይ በካርጎ አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን ሽልማቶችን ማግኘቱን የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል።

የአፍሪካ ምርጥ የፋርማ እቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ (Air Cargo Pharma Service of the Year, Africa) እና የአፍሪካ ምርጥ የዕቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ (Cargo Airline of the Year, Africa) ያገኛቸው ሽልማቶች ናቸው።

ሽልማቶቹ አየር መንገዱ ለልህቀት፣ ፈጠራ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለደንበኞች ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላክቱ ናቸው።

ዓለም አቀፍ የዕቃ ጭነት በረራ አድማስ በማስፋት በዓለም ደረጃ ያለውን ተፎካካሪነት አጠናክሮ እንዲቀጥል አበርክቶ እንዳለውም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት መዳረሻዎቹንና አገልግሎቶቹን በማስፋፋት የመሪነት ሚናውን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አየር መንገዱ በመረጃው አመልክቷል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *