የሕንድ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ልዑክ በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመን ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
ልዑኩ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሮች ዳጋቶ ኩምቤ እና ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ጋር በአዲስ አበባ ተወያይቷል።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ በፋርማሲቲካል፣ በጨርቃጨርቅ፣ በአይ ሲ ቲ፣ በግብርና እና ሌሎችም ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ልዑኩ ማሳወቁን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።
የሕንድ ንግድና ኢንቨስትመንት ልዑክ በኢትዮጵያ ለሚያከናውኑት ኢንቨስትመንት መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያድርግ ምክትል ኮሚሽነሮቹ አረጋግጠዋል።