የቱሪዝም ሚንስትር ዴዔታ ሌንሳ መኮንን ከኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ጋር በቱሪዝም ዘርፍ ዙሪያ በሚከናወኑ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
በውይይታቸውም÷ የጎብኚ ፍሰቱን ለመጨመር በቅንጅት ለመሥራት እና እስከአሁን እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
እንዲሁም እንደ “ET-Holiday” ዓይነት የጎብኚ ማበረታቻ መርሐ-ግብሮችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ የማሻሻያ ነጥቦች ላይ ተግባብተዋል።
በዓመት ከ 11 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን የሚያስተናግደው ዓየርመንገዱ÷ ደንበኞቹ ስለኢትዮጵያ የጎብኚ መዳረሻዎች መረጃ እንዲኖራቸውና የተለያዩ የሀገሪቱን አካባቢዎች እንዲጎበኙ ለማድረግ ብሎም አዳዲስ የቱሪዝም ፕሮሞሽን መንገዶችን ለመጠቀም በሚቻልበት አግባብ ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ