በቻይና ግዙፍ የዘመናዊ ስልክ አምራች የሆነው ዣኦሚ ኩባንያ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መስራቱን አስታውቋል።
የዣኦሚ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሊይ ዩን÷ በኩባንያው የተሰራው የመጀመሪያው የአሌክትሪክ መኪና ስፒድ አልትራ 7 (ኤስዩ7) የሚል የምርት መለያ ያለው ሲሆን 500 ሺህ ዩዋን ወይም 69 ሺህ 186 ዶላር ዋጋ እንደሚያወጣ ገልፀዋል።
መኪኖቹ ግዙፎቹ የቴስላ ኩባንያ እና ቢዋይዲ ከሚያመርቷቸው የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ጋር የሚፎካከሩ ስለመሆናቸውም ተናግረዋል።
ኩባንያው ለደንበኞቹ ከስልኮች፣ ከላፕቶፖች እና ከሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች በተጨማሪ የኤስዩ 7 የአሌክትሪክ መኪኖችን የሚያቀርብ ይሆናል ብለዋል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ የዣኦሚ ኩባንያ አዲሱን የኤሌክትሪክ መኪና በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረቡን የገለፀ ሲሆን፤ ይህም በሌሎች መኪና አምራች ኩባንያዎች ላይ ቅሬታን ማስነሳቱን ጠቁሟል።
የቢኤአይሲ ግሩፕ ኩባንያ የሆነው ዣኦሚ በዓለም ደረጃ ሶሰተኛው ግዙፍ የስልክ አምራች ኩባንያ ሲሆን ከስልክ እና ላፕቶፖች በተጨማሪ በዓመት እስከ 200 ሺህ መኪኖችን ለማምረት ማቀዱን ቢቢሲ ዘግቧል።